የ ፋሲካ ዕለት ሁሌ እንደምናደርገው ከእቶቼ ጋር walk አድርገን እየተመለስን ልክ ቅ/ማርያም ጋር ስንደርስ በመኪና ያሉ ወታደሮች"እናንተ ተራራቁ" ብለው ተቆጡን። እኛም ድንግጥ ብለን "ውይ እሺ! ግን እኮ ከአንድ ቤት ነው የወጣነው" አልናቸው። 1/11
ይህን እዳልናቸው በሚያስደነግጥ ፍጥነት ከመኪናቸው ዘለው ወርደው እየሮጡ ወደ እኛ መጡ የምር ሊመክሩን የመጡ ነበር የመሰለኝ! (በትህትና ማናገርም ያበሳጫል? )2/11
"እንዴ፣ ምን ልታደርገ ነው ስለው" አንዱ በጥፊ ሌላው በርጊጫ ሌላው ደሞ በዱላ ተረባረብብኝ! ታናናሽ እህቶቼ ደጋግመው ለመኗቸው! ግን ለእነሱ እንኳን አልራሩም፤ እነሱንም መቱዋቸው!3/11
የሚሆነውን ማመን አልቻልኩም። ያለምንኩዋቸው ልመና አልነበረም! ይሄ ሁሉ ሲሆን በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች ነበሩ። ልክ የቀረፃ ትእይንት እንደሚያይ ሰው ገልመጥ እያደረጉ ከማለፍ ያለፈ አንድም እንኳን እባካችሁ ያለ ሰው አልነበረም።4/11
ተከታታይ ዱላዎች እግሬ ላይ አረፉብኝ ። ጆሮዬ ላይ በሃይል ተመታሁ። እንደዛ ደብድበው ጥለውን ሲሄዱ ከህመሜ ባለፈ በዚህች ሀገር ላይ ጠባቂ አልባ መሆኔ፣ እንደፈለጉ እንዲያደርጉ የሚተዋቸው ህግ እንዳለ አስቤ ይበልጥ አለቀስኩ። 5/11
የተመታሁበት ቦታ እስከዛሬ ያመኛል። በእልህ እና በዱላው ምክንያት ሁለት ቀን በስርዓት እንቅልፍ አላገኘሁም። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ሃይ ባይ እንደሌላቸው ማመናቸው ይበልጥ አሳምሞኛል። 6/11
ከዩንፎርማቸው ላይ መፈራት እና ጭካኔ እንጂ በዜጎች ልብ ውስጥ የደህንነት ስሜት አለመፍጠሩ አሳዝኖኛል። (እነኛ ዝም ያሉት መንገደኞች ዝም ያሉት ጠያቂ አልባ ናቸው ብለው አይደል? ግን ያ መሆን አለበት? አይመስለኝም! ) 7/11
ወረርሽኝን ለመከላላከል ወታደር ለምን እዳስፈለገ አልገባኝም! እነዚህ ሰዎች ምንም አይነት ተጠያቂነት የለባቸውም! የት እንደሚጠየቁ አይታወቅም! ገለውም ቢሄዱም!! እንደዚህ አይነት ጥቆማ ለመቀበል የተዘጋጀው ስልክ አይነሳም!8/11
የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የሆነው ተስፋዬ ዳባ ጋር ስደውል «የማውቀውቅልሽ ነገር የለም» ብለው ጃሮዬ ላይ ስልኩን ዘጋው! ይሄ ነው ሕዝብን ማገልገል? ይሄ ነው የሕዝብ ተወካይ ማለት? 9/11
ማመልከቴ ለውጥ ላያመጣ ይችላል፣ ግን ደግሞ ዝም ማለት አልፈልግም። ነገ ከነገ ወዲያም እንዲህ እንዳሻቸው ያገኙትን ሰው እየደበደቡ ሊዘልቁ ነው።10/11
ቢያንስ በደሉን ውጦ ዝም የማይል ሰው እንዳለ፣ ቢያንስ እነሱም ሊጠየቁ እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው!11/11

#COVID19Ethiopia
#Ethiopia
You can follow @ruti_09.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled: